Skip to main content
003

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ አፈፃፀም ሪፖርት ከተጠሪ ተቋማት ጋር እየገመገመ ይገኛል። ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ሆሳዕና በመድረኩም የሠላምና ፀጥታ ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ቀርቦ ዉይይት ተደርጓል። በዕለቱም የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ እና ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ ፣ የክልሉ ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ ኮለኔል ተሻለ ኤረደዶ ፣ የክልሉ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አበበ ከበደ እና የሰላምና ፀጥታ ቢሮና የተጠሪ ተቋማት የማነጅመንት አባላትና የልማት ዕቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ግብረ መልስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች ተሳታፊ ሆነዋል። 

የቢሮዉ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ እንደገለፁት እንደተቋም በርካታ ተግባራት በዕቅድ መመራታቸዉን አስታዉሰዉ በበጀት ዓመቱ የአፈፃፀም ችግር ያለባቸዉን ተግባራት በመለየት የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ አካል በማድረግ ለተግባራዊነቱ በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል። ኃላፊዉ አክለዉ በ2019 በጀት ዓመት የህዝቡን ጥያቄዎች በተገቢና አሰራርን በጠበቀ መንገድ መፍታትና የፀጥታ ስጋት እንዳይሆን መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዉ በፀጥታ ምክር ቤት የተቀመጡ አቅጣጫዎችን የስልጣን የተዛባ አመለካከትና ሌብነትን የሚታገል ጠንካራ የፀጥታ መዋቅር ለመገንባት የተኬደበትን እርቀት በማስቀጠል የተሻለ ዉጤት ማምጣት እንደሚገባ አሳስበዋል። 

ተሳታፊ ተጠሪ ተቋማት በበኩላቸዉ ቢሮዉ በተሻለ የመፈፀም አቅም እንዳለዉ በሪፖርቱ የቀረበበት መንገድ በጠንካራ አፈፃፀም ላይ እንዳለና ተግባራት እየፈፀመ ያለበትን ቁመና በበለጠ ግንዛቤ የሰጠን መድረክ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል። ተሳታፊዎች አክለዉ ተግባራትን በዕቅድ ለመፈፀም ከፍተኛ የሆነ የበጀት እጥረት ለስራቸዉ ትልቅ ተግዳሮት እንደሆነባቸዉ በመጠቆም የሚመለከተዉ አካል ትኩረት ሰጥቶ የበጀት እጥረቱን ሊፈታ ይገባል። 

በመጨረሻም የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ከተደረገ በኃላ መሻሻል ያለባቸዉ ሀሳቦች ተስተካክለዉ እንዲቀርቡ ሀሳብ በማንሸራሸርና ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።