Skip to main content

ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከክልሉ ሕዝብና መንግስት የተሰጠውን የክልሉን ሰላምና ፀጥታ የማስከበር ተልዕኮ ለማሳካት ካደራጃቸው የስራ ክፍሎች መካከል የግጭት አፈታትና የህግ ጉዳዮች ክትትልና ድጋፍ ዘርፍ አንዱ ሲሆን ዘርፉ በሥሩ በሉት ዳይሬክቶሬቶች አማካኝነት የሚከተሉትን አገልግሎቶች ይሰጣል፡-

 

        ግጭት ጥናትና አፈታት ዳይሬክቶሬት               

  • የግጭት ይፈታልኝ አቤቱታና የመረጃ ግብዓቶችን በመጠቀም ግጭቶች ወደ ሁከትና ብጥብጥ ደረጃ ከመድረሳቸው በፊት መንስዔዎቻቸው ላይ የዘላቂ መፍትሄ ጥናት በማካሄድ መፍታት፤
  • በግጭት አስተዳደርና አፈታት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን መስጠት፣
  • ግጭቶች ወደ ሁከትና ብጥብጥ ከተሸጋገሩ እንዳይስፋፉ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ የማረጋጋትና የማስተዳር አገልግሎት ይሰጣል፤
  • ተመሳሳይ ግጭቶች እንዳይከሰቱ የችግሮቹን መንስኤ በመለየት ስትራቴጂክ እርምጃ እንዲወሰድ አማራጭ የመፍትሄ ሀሳቦችን ያቀርባል፤
  • ተመሳሳይ ግጭቶች እንዳይከሰቱ የችግሮቹን መፍትሄዎች ላይ የማህበረሰብ ውይይት በማድረግ ግጭቶችን በዘላቂነት የመፍታት አገልግሎት፤
  • በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወደ ቄአቸው እንዲመለሱ ባለድርሻና ተባባሪ አካላትን የማስተባበር አገልግሎቶችን ይሰጣል፤

የህግ ጉዳዮች ክትትልና የጸጥታ አካላት ማስተባበርያ ዳይሬክቶሬት

  • ከግጭት ጋር ተያያዥነት ያላቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንዲፈቱ ማድረግ፣
  • ከግጭት ጋር ተያያዥነት ያላቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንዲፈቱ ማድረግ፣
  • በግጭት ወቅት በፀጥታ አካላት በህፃናት፣በሴቶችና በአዛውንቶች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳይፈፀም መከላከል፤
  • በግጭት ሂደት የግጭት ተዋንያን የሆኑ አካላትንና ግለሰቦችን በህብረተሰቡ ተሳጽፎ በማጋለፅ በህግ አግባብ እንዲጠየቁ የማድረግ አገልግሎት፤

የአጐራባች ክልሎች አስተዳደር ወሰን አካባቢ ሕዝቦች ግንኙነት ማጠናከር ዳይሬክቶሬት

  • ክልሉ ከሚዋሰኑባቸው አስተዳደር ወሰን አካባቢ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ወይም የፀጥታ ችግሮችና አለመግባባቶችን በውይይት የመፍታት አገልግሎት፤
  • አስተዳደር ወሰን አካባቢ ያለውን ማህበረሰብ ግንኙነት በልማት በማስተሳሰር መልካም ጉርብትናን መፍጠር፤
  • በአስተዳደር ወሰን አካባቢ የሚገኙ ማህበረሰቦች መካከል የግንኙነት ሁኔታ በጥናትና ምርምር ለይቶ ዘላቂ ሠላምንና አብሮነትን የማሳደግ አገልግሎት፣
  • የአጎራባች ክልሎች የጋራ ምክክር ፎረም በማመቻቸት ለግንኙነት ምቹ ሁኔታ የመፍጠር አገልግሎት፤
  • በአስተዳር ወሰን አካባቢ ለፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የሆኑ አካላትን ለይቶ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ለሕግ አሳልፎ መስጠት፤
  • በአስተዳደር ወሰን አካባቢ ከተፈጠረ ግጭት ጋር ተያይዞ የተዘረፉ ንብረቶችን በህብረተሰቡ ተሳትፎ ለባለቤቶቻቸው እንዲመለሱ የማድረግ አገልግሎት፤
  • ለህብረተሰቡ በፌደራሊዝም እና በመንግስታት ግንኙነት ግንዛቤ የማስጨበጥና ሥልጠና የመሥጠት አገልግሎት፤