Skip to main content

                                                           የሴክተሩ ተግባርና ኃላፊነት፤

ሰላምን ለማስጠበቅ አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር ይሰራል፤ የክልሉን ሕዝብ ሰላም፣ ደህንነትና ነጻነት እንዲከበሩ የሚያስችል ስልት ይነድፋል፤ የግንዛቤና የንቅናቄ ሥራዎችን ያከናውናል፤
በተለያዩ ሃይማኖቶችና እምነቶች ተከታዮች መካከል ሠላምና መከባበር እንዲሰፍን ለማድረግና ግጭትንም ለመከላከል እንዲቻል አግባብ ካላቸው የመንግሥት አካላት፣ የሃይማኖት ተቋማትና ከሌሎች ማናቸውም አካላት ጋር በመተባበር ይሠራል፤
በተለያዩ ኃይማኖቶችና እምነቶች ተከታዮች፣ እንዲሁም በተለያዩ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል ሰላምና መከባበር እንዲሰፍን ለማድረግ አግባብ ካላቸው የመንግሥት አካላት፣ የባህልና የኃይማኖት ተቋማት፣ እንዲሁም ከሌሎች አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር ይሠራል፤
በክልሉ ውስጥ የሚንቀሣቀሱ የሀይማኖትና የእምነት ተቋማትን ይመዘግባል፣ ሰርትፍኬት ይሰጣል፣ ይከታተላል፣ ፈቃድ ያድሣል፣ ሕገ-ወጥ ሆኖ ሲገኝም ፈቃድ ያግዳል፣ ይሰዘርዛል፤
 ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር አገራዊ አንድነትና መግባባትን የሚያጎለብት የባህል ልውውጥ፣ የስነ-ዜጋ ትምህርት እና ኪነ-ጥበብ የሚስፋፋበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
የፀረ-ሰላም ኃይሎችን እንቅስቃሴ ይከታተላል፣ በዚህም የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ አሠራሮችን አጥንቶ ተግባራዊ ያደረጋል፣
በክልሉ በግለሰቦችና በቡድኖች መካከል የሰላም፣ የመከባበርና የመቻቻል ባህል እንዲዳብር የግንዛቤና ንቅናቄ ስልቶችን ይቀይሳል፣ አተገባበሩን ይከታተላል፤
በክልሉ ውስጥ ባሉ አስተዳደር እርከኖች መካከል የሚነሱ የማካለል ጥያቄዎች በሠላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ያደርጋል፣
የክልሉን የፀጥታ ሁኔታ በሚመለከት ጥናትና ክትትል ያደርጋል፣ የፀጥታ መረጃዎችን ይሰበስባል፣ ይተነትናል፣ ያሰራጫል ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል የክልሉን ሰላም ያረጋግጣል፣
የክልሉን የፖሊስ ኮሚሽን ሥራዎች በበላይነት ይመራል፣   ይከታተላል፣ ያስተባብራል፣
የክልሉን ሕዝብ ደህንነት፣ ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር  ተባብሮ ይሠራል፣
የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በአስቸኳይ በቁጥጥር ስር ለማዋል እንዲቻል ሲታዘዝ የፀጥታ ኃይል ያሠማራል፣
ክልሉ ውስጥ ዘመናዊ የሆነ የፀጥታ መረጃ ፍሰት አያያዝና አደረጃጀት እንዲኖር ስልት ይቀይሳል፣ ይተገብራል፣
በክልሉ በተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች ከብሔረሰቦች ማንነት ጋር ተያይዘው በሚነሱ የድንበር ማካለል ጉዳዮች በብሔረሰቦች ምክር ቤት የሚሰጡትን ውሣኔዎች ተግባራዊ ያደርጋል ፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
የፀጥታ መረጃ ለማሰባሰብና ለማስተዳደር የሚረዳ ልዩ የፋይናንስና የበጀት አስተዳደር እንዲሁም የሰው ኃይል አስተዳደር ደንብ በመስተዳደር ምክር ቤት ውሳኔ ተግባራዊ ያደርጋል፣
የፀጥታ መደፍረስ ወይም የተፈጥሮ አደጋ ሲከሰት በሚወሰደው የመከላከል እርምጃ በሴቶችና በህፃናት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የጥንቃቄ እርምጃ ይወስዳል፣
ከአጐራባች ክልሎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ፀጥታን በሚመለከት ግንኙነት ያደረጋል፣ በድንበር አከባቢ ያለውን ህብረተሰብ ግንኙነት እንዲሻሻልና እንዲጠናከር የሚረዱ ሥራዎችን ይሠራል፣
ሚሊሻውን ፀጥታን ለማስከበር በሚያስችል አኳኋን ያደራጃል፣ እንደአስፈላጊነቱ ከህዝቡና ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት የሚሰራበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
ክልሉ በሚያዋስናቸው ጐረቤት አገሮች ድንበር አካባቢ የግጭት ሁኔታ በመከታተል መረጃ ያሰባስባል፣ ግጭት እንዳይከሰት የመከላከል ሥራዎችን ይሠራል፡፡ ሲከሰትም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት መፍትሔ እንዲያገኙ ያደረጋል፣
የሚሊሽያ ኃይልን አቅም በመገንባት የህብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታ እንዲጠበቅ ያደርጋል፣
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በግጭት መነሻ ምክንያቶች ላይ ጥናትና ምርምር ያካሂዳል፣ የመፍትሔ ሃሳቦችና የአፈፃፀም ስትራቴጂዎችን ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣
ሚሊሺያው ለረጅም ጊዜ ከምርት ሥራው ሳይነጠል በፀጥታና ሌሎች መንግሥታዊ ሥራዎች ላይ እንዲሰማራ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
በክልሉ በሚገኙ የአስተዳደር እርከኖች መካከል ግጭቶች እንዳይነሱ የመከላከል ሥራዎችን ይሠራል፣ ሲከሰቱም በቁጥጥር ሥር ያውላል፣ የግጭቱን መንስዔ አጣርቶ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣
በክልሉ የሚከናወኑ የወሳኝ ኩነቶች ተግባራትን በበላይነት ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣ ይከታተላል አፈጻጸሙንም ይገመግማል፣
 
ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡