የሰላም ግንባታና ብዝሃነት አያያዝ ዘርፍ በውስጡ ሁለት ዳይሬክቶሬቶች ያሉት ሲሆን የሚሰጡትም አገልግሎቶች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
በሰላም እሴት ግንባታ ዳይሬክቶሬት የሚከናወኑ ተግባራት
- የፍላጎትና የክፍተት ዳሰሳ ጥናት የማካሄድ፤
- የህብረተሰቡን በሰላም አብሮ የመኖርና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ባህልን የማጎልበት፣
- የአሰራር ስርዓትና የሥልጠና ሰነዶችን የማዘጋጀት አገልግሎት፣
- በሰላም ግንባታ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎችን፣ ሴሚናሮችንና ወርክሾፖችን ማዘጋጀት፤
- ቀጣይነት ያለው የማህበረሰብ ተኮር የምክክር መድረኮችን የማመቻቸትና የማስተባብር፣
- የሰላም እሴትን የማስረጽና የማጎልበት አገልግሎት፣
- የንቅናቄ መድረኮችን በማዘጋጀት ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በሰላም ዙሪያ በባለቤትነት እንዲሰለፉ የማድረግ፣
- ማናቸውም የልማትና የማህበራዊ አገልግሎት ሥራዎች ሰላምን የሚያጎለብቱና የግጭት ተጋላጭነትን የሚቀንሱ መሆናቸውን የመከታተል፣
- የሰላም አደረጃጀቶችን በማህበረሰቡና በትምህርት ተቋማት የማደራጅትና የማጠናክር፣
- የህብረተሰቡን ጠቃሚ የሰላም እሴቶችንና የአኗኗር ዘይቤዎችን የማዳብር፣
- ብሔራዊ መግባባትንና ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር የብሔራዊ በጐ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ተሣታፊ ወጣቶችን የመመልመል፣ የማሰማራትና ክትትል የማድረግ፤
- በህትመትና በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች የሰላም ባህል ግንባታን የማጎልበት
- መረጃ የማሰባሰብ፣ የማደራጀትና ጥቅም ላይ የማዋል
- ክትትል፣ ድጋፍና ግብረ መልስ የመስጠት፤
- ምርጥ ተሞክሮዎችን የመቀመርና የማስፋት ተግባራት ናቸው፡፡
በሀይማኖትና እምነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የሚከናወኑ ተግባራት
- ሃይማኖት ነክ ቅሬታዎችና አቤቱታዎችን እንዲሁም የአሠራርና የአደረጃጀት ክፍተቶችን መነሻ በማድረግ፣
- የፍላጎትና የክፍተት ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ፤
- የአሰራርና የሥልጠና ሰነዶችን የማዘጋጀትና ለተጠቃሚ የማዳረስ፣
- በሀይማኖትና እምነት ተቋማት እንዲሁም በተከታዮቻቸው መካከል የአብሮነት፣ የመቻቻልና የመከባበር እሴቶች እንዲዳብሩ የግንዛቤ ማስጨባጫና የሥልጠና ሥራዎችን የሚያከናውን፣
- አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ምላሽ የመስጠት፣
- የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬትን በማረጋገጥ ድጋፍ መስጠት፣
- የሀይማኖት ተቋማት ጉባዔዎችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የማጎልበት፤ የመደገፍ፣ የማጠናከር፣የመከታተልና የማብቃት፣
- በሀይማኖት ሽፋን የሚፈጸሙ የአክራሪነትና ጽንፈኝነት አመለካከት ችግሮች እንዳይከሰቱ የሚከላከል፣
- የሀይማኖትና እምነት ተቋማት በህግ አግባብ እንዲመሩ የሚሰራና፣
- የሃይማኖት ነክ መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የመተንተን፣ የማደራጀትና ጥቅም ላይ የማዋል አገልግሎት፣
- ክትትል፣ ድጋፍና ግብረ መልስ መስጠት፤
- ምርጥ ተሞክሮዎችን የመቀመርና የማስፋት ተግባራት ናቸው፡፡