በፀጥታ መረጃ አሰባሰብ፣ አቅርቦት፣ አስተዳደርና ምላሽ አሰጣጥ ዘርፍ የሚሰጡ ዋና ዋና ተግባራት
ዋና ዋና ተግባራት
- ዕቅድ ማዘጋጀትና የአፈጻጸም ሪፖርት ማቅረብ
- የፍላጎትና የክፍተት ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ
- የአደረጃጀት፣ የአሰራርና የስልጠና ሰነዶችን አዘጋጅቶ ለሚመለከተዉ አካል ተደራሽ ማድረግ
- ሥልጠናዎችን የመስጠትና የንቅናቄ መድረኮችን በማዘጋጀት ግንዛቤ ማስጨበጥ
- አካባቢያዊ የግጭት ቅድመ-ማስጠንቀቂያ አመላካቾችን በጥናት በመለየት፣ መቅረጽና መከታተል፣
- የፀጥታ ስጋት ሁኔታ ጥናት ማካሄድ
- የግጭት ቅድመ-ማስጠንቀቂያ መረጃና ፈጣን ምላሽ አደረጃጀቶችን ማደራጀትና ማጠናከር፣
- የስጋት መስኮችን፣ ቀጠናዎችንና የመረጃ ምንጮችን መለየት፤ ተባባሪ መመልመል፣ ስልቶችን መዘርጋትና ተልዕኮ መስጠት፣
ዋና ዋና ተግባራት
- የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ከአስተዳደራዊ፣ ከመገኛኛ ብዙኃን፣ ከሰላምና ፀጥታ፣ ከኢኮኖሚ፣ ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃምና ከማህበራዊ ሁኔታ ላይ ማሰባሰብ፣ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ፣ መተንተን እና ማሰራጨት፣
- የፀጥታ መረጃ መሰብሰብ፣ መተንተንና ማደራጀት፣
- የተደራጁ ወንጀሎችንና ህገ-ወጥ ድርጊቶች ላይ በልዩ ተልዕኮ በስውር ክትትል የማድረግ፣ መረጃ የመሰብሰብ እና ጥቅም ላይ እንዲዉል ማድረግ፣
- ግጭትን ለመከላከልና ለማስቆም በግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ መረጃ መሠረት ፈጣን ምላሽ መስጠትና ማስተባበር፣
- በግጭት አዝማሚያ መነሻነት የሚቀርቡ ቅሬታዎችና አቤቱታዎችን አጣርቶና ትክክለኛነቱን አረጋግጦ መረጃን ከመፍትሄ ሀሳብ ጋር ለሚመለከተዉ አካል ማስተላለፍ፣
ዋና ዋና ተግባራት
- መረጃዎችን በመረጃ ቋት ለመያዝ የሚያስችል የመረጃ ቴክኖሎጂ አሰራር ስርዓት መዘርጋት፣ መረጃዎችን ማደራጀትና ማስተዳደር፣
- የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ ዑደት እና ፈጣን ምላሽ ማስተባበር፣ አፈጻጸሙ ላይ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
- የህግ ማዕቀፎችና የአሰራር ስርዓቶች የማዘጋጀትና መተግበራቸውን መከታተልና መደገፍ፣
- መሰረታዊ መረጃ መሰብሰብ፣ ማጠናቀርና ማደራጀት፣
- መልካም ተሞክሮን መቀመርና ማስፋት
- የፋይዳ ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ
- ክትትል፣ ድጋፍ፣ ግምገማና ግብረመልስ መስጠት፣