እንኳን ወደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሰላምና ፀጥታ ቢሮ በደህና መጡ!
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሰላምና ፀጥታ ቢሮ የክልሉ መንግስት በአዲስ መልክ ሲቋቋም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 199/2015 ዓ/ም መሠረት በአዲስ መልክ የተቋቋሙ የክልል ተቋማት መካከል አንዱ ነዉ፡፡ ቢሮው በአዲስ መልክ ሲደራጅ በክልሉ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ማስፈን፣ ክልላዊ መግባባትና አንድነትን ማጠናከር፣ የህግ የበላይነትን ማስከበር፣ ዘመናዊ የፀጥታ መረጃ ፍሰት እንዲኖር፣ በክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ጥናትና ክትትል ማድረግ፣ በክልሉ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም በተለያዩ ኃይማኖትና እምነት ተከታዮች መካከል ሰላምና መከባበር እንዲሰፍን ከሚመለከታቸው መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በትብብር መሰራትን ያካትታል፡፡
በዚህ ድህረ ገፅ ላይ ቢሮዉ ሰላምን በማፅናትና የህዝቡን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ በመገንባት የሰላሙ ባለቤት ህዝቡ እንዲሆን በማስቻል የቢሮዉ የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ እቅደችን በማዘጋጀትና አጠቃላይ የሰላም እና ደህንነትን በማረጋገጥና በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር ማእቀፎችን በመፍጠርና በመተግበር ረገድ ትልቅ ሚና በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡
ቢሮዉ በሀገር ዉስጥና ከሀገር ዉጪ ሆነዉ ለሠላም ከሚሠሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች ለአረጋዊያን ለህፃናትና ሴቶች በሚደረገዉ እንክብካቤ ዙሪያ ቢሮ በተደረጀ መልኩ በቅንጅት የሚሠራ ሲሆን የሰዉ ልጆች ሰብኣዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ሳይሸራረፍ እንድረጋገጥ በጥብቅ ዲሲፕሊን ይሠራል።
ቢሮዉ ክልሉ ለቱሪዝም፣ ለኢንቨስትመንት እና ለሥራ ዕድል ምቹ እንዲሆን ሠላምን በማረጋገጥ ዜጎች ያለ ምንም ስጋት 24 ሰዓት ያለ ገደብ በነፃነት የሚንቀሳቀሱበት ክልል በማድረግ ለሀገር ሠላምና የኢኮኖሚ ዕድገት አጋዥና ዐቅም የሚሆን በተግባር የተረጋገጠ ሠላም ለማስፈን ተሠርቷል። በሂደቱም ተጨባጭ ዉጤት የተረጋገጠ ሲሆን በቀጣይም ተጠናክሮ እየተሰራ ይገኛል፡፡
በተጨማሪም ህዝብን ከአደጋ እና ስጋት የመጠበቅ፣ የህግ የበላይነትን የማስፈን፣ ከፌዴራልና ከክልል አስፈጻሚ አካላት እንዲሁም ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ተልዕኮው ተመጋጋቢና ትስስር ያለው ውጤታማ እንዲሆን በማድረግ ላይ ነዉ፡፡
ቢሮዉ የፀጥታ ስራዉን ሲያከናዉን የሰላሙ ባለቤት ከሆነው ህብረተሰብ፣ ከባለድርሻ አካላትና ተባባሪ ወገኖች ጋር ይበልጥ ተጠናክሮ በመንቀሳቀስ የክልሉን ሰላም፣ ፀጥታና የህዝብ ደህንነት የማረጋገጥ ተግባር ለማስቀጠል የሚያስችል ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል ስለዚህ ድህረ ገፃችንን እንዲጎበኙ እና የሰጠነዉን መረጃ እንዲያገኙ እየጋበዝን ስለ ይዘቱ እና ስለ ድህረ ገፁ ለሰጡን አስተያየት እናመሰግናለን።
አቶ ተመስገን ካሳ
የቢሮዉ ኃላፊ