Skip to main content
004

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ እና የቡኢ ከተማ አስተዳደር አሁናዊ የጸጥታ ሁኔታ ተገመገመ። ሰኔ 20/2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳና የቡኢ ከተማ አስተዳደር አሁናዊ የጸጥታ ሁኔታ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዝርዝር ተገምግሟል።

የውይይት መድረኩ የመሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ እና አቶ እንዳለ ወ/አማኑኤል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሰላም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ፣ሲሆኑ በመድረኩ ላይ የተገኙት አቶ ተካልኝ ንጉሴ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ፣የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አመራሮች፣የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ በቴ፣የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ እንዲሁም የክልሉ አድማ ብተና አመራሮችና የወረዳው እና የቡኢ ከተማ አስተዳደር የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በቡኢ ከተማ ውይይት ተካሂዷል።

በመድረኩም ሰፊ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ከተደረገ በኃላ የጋራ መግባባት ተደርሶ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል። ዘገባው የሶዶ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።